የመድረክ መሪ ተቃዋሚዎች አንድነት እንዲፈጥሩ አሳሰቡ

ትልቁ የተቃዋሚዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ በሚባለው ተቋም ውስጥ ለተሰበሰቡ ታዳሚዎች ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና

Your browser doesn’t support HTML5

የመድረክ መሪ ተቃዋሚዎች አንድነት እንዲፈጥሩ አሳሰቡ - ውይይት ከዶ/ር መረራ ጉዲና ጋር - ክፍል 1

ትልቁ የተቃዋሚዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ በሚባለው ተቋም ውስጥ ለተሰበሰቡ ታዳሚዎች ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

የዶ/ር መረራ ወረቀት ርዕስ፡- የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር አንድ እርምጃ ወደፊት፤ ሁለት እርምጃ ወደኋላ” የሚል ነው፡፡

ዶ/ር መረራ በዚህ ፅሁፋቸው ውስጥ ያለፉት 23 የኢሕአዴግ ዓመታት በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ፡…ያልተሣኩ ነበሩ…” ብለዋል፡፡

በ23ቱ ዓመታት መጀመሪያ ላይ የተነሡት ሥሉስ ቃላት - “ጎሣን መሠረት ያደረገ ፌደራላዊ ሥርዓት፤ ብዝኀ ፓርቲ ዴሞክራሲና የነፃ ገበያ ምጣኔ ኃብት - አልተከበሩም፤ የከሸፉ ቃላት ሆነዋል” ብለዋል፡፡

መጭውን ምርጫ አስመልክቶ ዶ/ር መረራ ሲናገሩ ተቃዋሚዎች በቀረው ጊዜ ተቃዋሚዎች እንዲተባበሩና ጥንካሬን እንዲፈጥሩ መክረዋል፡፡

ከዶ/ር መረራ ጉዲና ጋር የተደረገውን ውይይት የመጀመሪያ ክፍል ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡