“የኦሞ ህፃን፡ ወንዙና ዱሩ የሚናገረው ታሪክ”

Your browser doesn’t support HTML5

በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርንያ ክፍለ-ግዛት የሚገኝ ጥናታዊ ፊልም አዘጋጅና ፕሮዲዩሰር በኢትዮጵያ ኦሞ ወንዝ አከባቢ በሚኖሩ ኅብረተሰብ ባሕልና ልምድ “የተረገሙ” ናቸው ተብለው በሚታመኑ ሕፃናት ላይ የሚፈፀመውን ግድያ የተመለከተ ጥናታዊ ፊልም ሠርቷል። የአካባቢው ተወላጅ የሆነ አንድ ወጣት ይህን ልምድ ለማስቀረት የሚያካሂደውን ዘመቻ የተመለከተም ጥንቅርም በዘጋቢ ፊልሙ ውስጥ ተካቷል።