ሙስና በኢትዮጵያ ያለበት ደረጃ እና የደቀነው አደጋ ክፍል -1

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ለሙስና ወንጀሎች ያላት ተጋላጭነት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን፣ “ትራንስፓረንሲ ኢንተረናሽናል” የተባለው ሉላዊ ተቋም ይገልጻል፡፡

የአሜሪካ ድምፅም ቀደም ሲል በጉዳዩ ላይ ጋብዞ ያወያያቸው እንግዶችም፣ በመንግሥታዊ የአገልግሎት መስጫዎችና በሌሎችም ዘርፎች ሙስና እየተባባሰ መኾኑን አመልክተዋል፡፡

አሁንም በኢትዮጵያ ሙስና ያለበትን ኹኔታ በተመለከተ፣ የአሜሪካ ድምፅ እንግዶችን ጋብዞ አወያይቷል፡፡

ተወያዮቹ የ“ትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ” ዋና ዲሬክተር አቶ ሳሙኤል ካሳሁን፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ እና በፍትሕ ሚኒስቴር በሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ አቶ ገብረ እግዚአብሔር ወልደ ገብርኤል ናቸው፡፡

የአወያያቸው አስማማው አየነው ነው፡፡ ክፍል አንድን ከተያያዘው ድምፅ ያዳምጡ፡፡