በድሬዳዋ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች የእንቅስቃሴ ገደብ

Your browser doesn’t support HTML5

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ከስራ መውጫ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ጀምሮ እስከ ንጋቱ አንድ ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ሙሉ በሙሉ እንዳይንቀሳቀሱ የሚከለክል መመሪያ ይፋ አደረገ።

መመሪያው ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የመመሪያው ዋነኛ ዓላማም የፌዴራል መንግሥት ከሐምሌ ጀምሮ ለመንግስት ተሽከርካሪዎች የሚያደርገውን የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ እንደሚያነሳ በማስታወቁ ከወዲሁ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም ለመጀመር ነው ተብሏል።