በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አለመረጋጋት ሚና ነበራቸው በተባሉ ተማሪዎች የዲሲፕሊን እርምጃ ተወሰደ
Your browser doesn’t support HTML5
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው አለመረጋጋት ላይ ሚና ነበራቸው ያላቸው ተማሪዎች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ። በቀጣይም ተጠያቂ የሚሆኑ ተማሪዎች እንደሚኖሩና በመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ላይም ማጣራት እየተደረገ ነው ብለዋል። ህይወታቸው ካለፉ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ተማሪዎች ላይም ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ህዝብ ግንኙነት አስታውቋል።