የዘይት ወረፋ - ድሬዳዋ

Your browser doesn’t support HTML5

ዛሬ ድሬዳዋ ላይ የታየው በአንድ ሊትር 48 ብር የሚያወጣውን ዘይት ከነጋዴዎች ከመግዛት በመንግሥት ሊትሩ በ26 ብር ሂሳብ የሚቀርበውን ዘይት ለመግዛት የተያዘ ወረፋ ነው፡፡ ቀኑን ሙሉ ወረፋ ይዘው ሳይደርሳቸው ለነገ የተቀጠሩም አሉ፡፡ ለአንድ ቤተሰብ በሽያጭ የሚቀርበው ከፍተኛው መጠን 5 ሊትር ነው፡፡
ኢትዮጵያ /SNV/ በተባለው ግብረሰናይ ድርጅት መረጃ መሰረት በ2005 ላይ 50 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የነበረው ዓመታዊ የምግብ ዘይት ግዢ በፍጥነት አድጎ 15 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ወስጥ ነው 400 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ደርሷል፡፡
በሌላ በኩል ባሰሳለፍነው የበጀት ዓመት 350ሺ ቶን ገደማ ሰሊጥ ወደውጭ ተልኮ 500 ሚሊዮን ዶላር ገደማ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አምና ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል፡፡ ሃገረቱ ግን ከዚህ ከዕጥፍ በላይ ሰሊጥ የማምረት አቅም ሁሉ አላት፡፡ ሆኖም በዘርፉ ላይ የሃገር ውስጥ የዘይት ገበያን ለመሸፈን የሚያስችል በቂ ሥራ ባለመሰራቱ ሃገሪቱ ባለፉት ዓመታት ሰሊጥ እየሸጠች ዘይት እየገዛች ትገኛለች፤ የዘይት አቅርቦቱም ወጥነት የሌለው በመሆኑ ዕጥረት እና የዋጋ መናር የሚስተዋልበት ነው፡፡