የኮቪድ-19 ቀድመ ጥንቃቄ በድሬዳዋ

Your browser doesn’t support HTML5

የድሬዳዋ አስተዳደር በከባድ ጭነት መኪኖችና ሌሎችም አሽከርካሪዎች አማካኝነት ኮሮናቫይረስ ከጎረቤት ሃገሮች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባና እንዳይሠራጭ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል። መዳረሻቸውን ድሬዳዋ ያደረጉ የ150 ከባድ መኪኖች እና ሌሎችም አሽከርካሪዎች በተለየ ማቆያ እንዲቆዩ እንደሚደረግ የጤና ቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ ለቪኦኤ ገልፀዋል። ድሬዳዋን አቋርጠው ወደመሃል አገር የሚሄዱ ተሽከርካሪዎችም አስፈላጊው የጤና ምርመራና ትምህርት እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።