የድሬዳዋ ዓመታዊ በጀት ጉዳይ
Your browser doesn’t support HTML5
የድሬዳዋ አስተዳደር በህገመንግሥቱ መሰረት ክልሎችና የፌዴራል መንግሥት የሚያካሂዱት የገቢ ክፍፍል ለድሬዳዋም ተግባራዊ እንዲሆን መጠየቁንና በዚህም ተስፋ ሰጪ ምላሽ እያገኙ መሆኑን የአስተዳደሩ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮ ኃላፊው አቶ ሱልጣን አሊዪ ከቪኦኤ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት የዚህ ተግባራዊነት ድሬዳዋ በዓመታዊ በጀቷ ላይ ትርጉም ያለው ጭማሪ እንድታገኝ ያስችላታል ብለዋል።