የማኅበራዊ ትረስት ፈንድ በኬንያ ናይሮቢ ተጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በውጪ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የቀረበዉ "በአንድ ቀን አንድ ዶላር ጥሪ" ዛሬ በኬንያ በይፋ ተጀምሯል። ናይሮቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በተደረገዉ ዝግጅት ላይ በኬንያና በአካባቢዋ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈዉበታል። በዝግጅቱ ላይ የኬንያ ማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ተወካይ በኬንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ና የፈደራል መንግሥት ተወካዮች ተገኝተዋል።