ከማላ ኸሪስ የምክትል ፕሬዚዳንትነት ዕጩነቱን ተቀበሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ትናንት ረቡዕ ለሦስተኛ ቀን በተካሄደው የዲሞክራቶች ጠቅላላ ጉባኤ ምሽት የካሊፎርኒያዋ ሰኔተር ከሚላ ኸሪስ የዕጩ ፕሬዘዳናት ጆ ባይደን አጋር ሆነው የተሰየሙበትን የምክትል ፕሬዚዳንትነት ዕጩነት ተቀብለዋል፡፡ በምሽቱ ተናጋሪዎች ከተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም በየሰው እጅ ባለው ጠመንጃና ሽጉጥ የሚደርሰው ጥቃት የአየር ጠባይ ለውጥ እና ኮቪድ-19 ዋነኞቹ ነበሩ፡፡