ባይደን የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩነትን ተቀበሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በመጨረሻም በትናንትናው ምሽት ዴሞክራቶች የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን ዕጩ ፕሬዘዳንታቸው አድርገው በይፋ ሰይመዋል፡፡ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ በልዩ ሁኔታ በተቀናበረው የድረ-ገጽ ላይ ዝግጅት ሲካሄድ በቆየው የዲሞክራቶች ኮንቬሽን ከዴሞክራቶችም ሆነ ሪፖብሊካን በፕሬዚዳንት ትረምፕ ላይ የተሰነዘሩ ትችቶች ተሰምተዋል፡፡ የጆ ባይደንን ሰብእና እንደ አባት፣ እንደ ባልም ሆነ የህዝብ አገልግጋይ የሚያወሱ ታሪኮችም ተደምጠዋል፡፡