ከወለጋና ምሥራቅ ሸዋ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን መጠለላቸውን የተናገሩ ተፈናቃዮች እየጣለ ባለው የበልግ ዝናብ ምክንያት ችግራቸው መባባሱን አስታውቀዋል።
ተፈናቃዮቹ በቂ ምግብና ልብስ እንደሌላቸውም ተናግረዋል።
ተፈናቃዮቹን ለማስተናገድ የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ መጠለያ ከተማው ውስጥ እንደሌለ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
ሰላሣ ሽህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ሁለት ካምፖችና በአራት አነስተኛ ማረፊዎች ላይ እያስተናገደ መሆኑን አስተዳደሩ አመልክቶ ተፈናቃዮቹን ችግሩን ደጋግሞ ቢያሳውቅም ትኩረት እንዳልተሰጠው ገልጿል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።