የፓኪስታን ሁለተኛዋ ትልቋ ከተማ ላሆር ውስጥ ዛሬ ጠዋት በአንድ ሃይማኖታዊ ቅዱስ ሥፍራ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ስምንት ሰዎች ሲገደሉ ከሃያ በላይ መቁሰላቸው ተገለጠ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የጥቃቱ ዒላማ ከቤተ ዕምነቱ መግቢያ በሮች አንዱ አቅራቢያ የቆመ የፖሊስ መኪና እንደሆነ ተገልጿል። የፐንጃም ክፍለ ሃገር ባለሥ።ጣን እንደገለጹት ከሞቱት መካከል ቢያንስ አምስቱ ፖሊሶች ናቸው።
በአስራ አንደኛው ክፍለ ዘመን የተገነባውና በሃገሪቱ በትልቅነቱና በጎብኝ ብዛት አንደኛ ነው የተባለው የሱፊ እስልምና ቅዱስ ስፍራ ከአሁን ቀደምም የቦምብ ጥቃት ደርሶበታል። እኤአ በ2010 በደረሰ የቦምብ ጥቃት አርባ ሰዎች ሞተዋል፡፡