ምዕራብ ጃፓን ውስጥ ከባድ የመሬት መናወጥ ደርሶ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሞቱ ። ከሁለት መቶ የሚልጡ ደግሞ ቆስለዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ምዕራብ ጃፓን ውስጥ ከባድ የመሬት መናወጥ ደርሶ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሞቱ ። ከሁለት መቶ የሚልጡ ደግሞ ቆስለዋል።
በመለኪያው ላይ ሥድስት ነጥብ አንድ ያስመዘገበው የመሬት መናወጥ ሁለተኛዋ የጃፓን ትልቁዋ ከተማ ኦሳካ አቅራቢያ የደረሰው ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ መሆኑ ታውቁዋል። በዛሬው የመሬት መናወጥ ምክንያት ከውቅያኖስ የሚነሳ ከባድ ጎርፍ (ሱናሚ) አደጋ ማስጠንቀቂያ አልተከተለም።
ከሰባት ዓመታት በፊት በደረሰው ከባድ የመሬት መናወጥና ሱናሚ በሺዎች የምቆጠሩ ሰዎች ማለቃቸው እና የፉኩሺማው የኒውክሊየር ሃይል ማመንጫ ጣቢያም እደጋ መድረሱ ይታወሳል ።