የንጉስ ሃላላ ድንጋይ በዩኔስኮ ዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ እንቅስቃሴ ተጀምሯል

Your browser doesn’t support HTML5

በዳውሮ ዞን የሚገኘው የንጉስ ሃላላ የድንጋይ ካብ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ እንቅስቃሴ መጀመሩን አንድ የዞኑ የሥራ ኃላፊ አስታወቁ። ካቡ የዳውሮ ህዝብ መለያና የጥንት ታሪኩ ምልክት እንደሆነም ተናገሩ። በገበታ ለሃገር እንዲለሙ ዕቅድ ከተያዘላቸው የኮይሻ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።