በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ የነበረ ግጭት መብረዱ ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተከስቶ የነበረ የተማሪዎች ግጭት መብረዱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ለታ ተስፋዬ ገልፀዋል። ከትናንት በስተያ ሰኞ አንድ ተማሪ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ መገደሉንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። በመቱ ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎች ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ውይይት መካሄዱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል::