የሰላሣኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያዎች ተጠናቀቁ፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
ኮንጎ ዲሪ፣ ጋና፣ ኢኳቶሪያል ጊኒና አይቮሪ ኮስት ለግማሽ ፍፃሜ አለፉ፡፡
በአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ አስተናጋጇ ኢኳቶሪያል ጊኒ ፈፅሞ ያልተጠበቀ ውጤት እያስመዘገበች ነው፡፡
ለሩብ ፍፃሜ ስምንቱን ቡድኖች መቀላቀሏ ሲያስገርም ትናንት የአፍሪካ “ጠንካራ ቡድን” የሚባለውን ቱኒዝያን 2 ለ 1 አሸንፋ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፋለች፡፡
የኪንሻሳው የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ቡድን የብራዛቪል አቻውን የኮንጎ ሪፐብሊክ ቡድን 4 ለ 2 ሸኝቶ ለፍፃሜ ካለፉት አንዱ ሆኗል፡፡
ሌሎች የግማሽ ፍፃሜ አላፊዎች ከሚለዩበት አንዱ በሆነው ጋና እና ጊኒ ባደረጉት ግጥሚያ ጋና በቀላሉ 3 ለባዶ አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉትን ሁለቱን ቡድኖች ተቀላቅሏል፡፡
በተከታዩ ግጥሚያ አይቮሪ ኮስት ጋናን 3 ለ 1 አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡ አይቮሪ ኮስት ሦስተኛውን ጎል ያስቆጠረው በባከነ ሰዓት ጭማሪ ሁለተኛው ደቂቃ ላይ ነው፡፡
ለተጨማሪ የሰሎሞን ክፍሌን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡