ቃለ ምልልስ ከባህልና ማኅበረሰብ እንግዳ፥ ገጣሚ ዓለማየሁ ታዬ ጋር።

ልክ እንደኛው ቅኔ የእኛን ቅኔ በሁለት መንገድ እንደምትተረጉመው ሁሉ፤ ሃይኩንም አንብበህ በሁለት መንገዶች ነው የምትተረጉመው። የቡድሂዝምን ፍልስፍናና አስተምህሮ አውቀህ ሃይኩን ስታነብና ሳታውቅ ስታነብ የተለያየ ትርጉም ነው የሚሰጥህ።

«የዓለማየሁ ሩባያት፤» «ሃይኩ፤» እና «ግራፊቲ፤» በሚል ርዕስ ለህትመት በበቁ ሶስት የግጥም መፃህፎቹ መነሻነት ለእንግድነት ከጋበዝነው ወጣቱ ገጣሚ ዓለማየሁ ታዬ ጋር የጀመርነው ውይይት ሁለተኛና የመጨረሻ ክፍል ቃለ ምልልስ በሃይኩና ግራፊቲ ላይ ያተኩራል።

የአስራ ስድስተኛውን ክፍለ ዘመን ጃፓናዊ ባለ ቅኔ ባሾን፥ ባለ ሦሥት መስመሯን ሃይኩንና የቡድሃ ዕምነት ፍልስፍናን ምን ያገናኛቸው ይሆን?

ዓለማየሁ «እንዴታ!» ይላል።

ባህልና ማኅበረሰብን ያድምጡ።