የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አደጋ እንደተጋረጠበት ተጠቆመ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) መካከል፣ ባለፈው ጥቅምት ፕሪቶርያ ላይ በተፈረመው የሰላም ስምምነት አተገባበር ላይ ታይተዋል የተባሉ ክፍተቶች ካልተፈቱ፣ ሒደቱን አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።

የአፍሪካ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት፣ አደረግኹት ባለው ክትትል፣ በሰላም ስምምነቱ ይዘት እና ስፋት፣ እንዲሁም በትግበራው ሒደት ላይ የተለያዩ ክፍተቶችን እንደተመለከተ ገልጿል፡፡

የጥምረቱ አባል ድርጅት የኾነው “አትሮሲቲስ ዋች አፍሪካ” ዋና ዳይሬክተር ዲስማስ ንኩንዳ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ በክትትሉ ከተለዩት ክፍተቶች መካከል፥ የኤርትራ ሠራዊት አሁን ድረስ ከትግራይ አለመውጣቱ፣ የተፈናቃዮች ኹኔታ ዘላቂ መፍትሔ አለማግኘቱ፣ ለአወዛጋቢ አካባቢዎች እልባት አለመሰጠቱ እና የሰላም ስምምነቱ የሚመለከታቸውን ሌሎች ባለድርሻዎች አለመካተቱ የሚሉት እንደሚገኙባቸው ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ፥ ፈራሚ አካላት ስምምነቱን እንዲያከብሩና ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር፣ የአፍሪካ ኅብረት ጥረት እንዲያደርግ፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረቱ ጥሪ አቅርቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።