ዋሽንግተን ዲሲ —
ሴናተር ቴድ ክሩዝ(Ted Cruz)በአየዋ (Iowa) የሪፐብሊካን ፓርቲውን እጩ ተወዳዳሪዎች ምርጫ ውድድር አሸነፉ። በመጪው ሳምንት በኒው ሃምፕሸር (New Hampshire) ከደገሙት፥ ፓርቲውን ወክለው ለፕሬዘዳንትነት ይወዳደራሉ።
በዲሞክራቲክ ፓርቲው በኩል ግን በቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን (Hillary Clinton) እና በርኒ ሳንደርስ (Bernie Sanders) መካከል የተካሄደው ውድድር በእኩል ድምፅ ተጠናቋል። ውጤቱ በሁለቱ መካከል የሚኖረው የቅድመ ምርጫ ሂደት የረዥም ጊዜ ትግል ሊሆን እንደሚችል አመላክቷል።
የአሜሪካ ድምፅ ብሄራዊ ዘጋቢ ጅም ማሎን (Jim Malone) ከደ ሞይን (Des Moines) የላከው ሪፖርት አለ።
ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5