በኢትዮጵያ የሚታሠሩ ጋዜጠኞች ቁጥር መጨመሩን ሲፒጄ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ መሻሻል አሳይቶ የነበረው የኢትዮጵያ ሚዲያ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን እና በተለይ ለእስር የሚዳረጉ ጋዜጠኞች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መጨመሩን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ሲፒጄ አስታውቋል።

ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የፕሬስ ነፃነት ቀን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የሚዲያ ባለሞያዎችም መንግሥት ጋዜጠኞችን ለችግሮች የመፍትሄ አካል ማረግ እንጂ ማሰር እንደሌለበት ጠቅሰው በተለይ ከማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሆን ተብሎም ይሁን ባለማወቅ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች መጨመር ሊታሰብበት እንደሚገባ ተናግረዋል።