አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ጥብቅ መመሪያ

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናይትድ ስቴትስ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ኦሚኮርን በሃገሪቱ መገኘቱ ካረጋገጠች ከ24 ሰዓት በኋላ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ ዓለም አቀፍ ተጓዦችን በተመለከተ ጥብቅ መመሪያዎችን ያወጡ ሲሆን በሃመላው ሃገሪቱ በመጓጓዣዎች ላይ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መመሪያዎችም ለተራዘመ ጊዜ እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ በተጨማሪም 200 ሚሊየን የኮቪድ 19 ክትባቶች በቀጣይ ወር ለሌሎች ሃገራት እንደሚለገሱም ቃል ገብተዋል፡፡