ሳዑዲ ዓረቢያ እገዳዎችን ልታነሳ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል

ሳዑዲ ዓረቢያ ኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ካጸናቻቸው የእንቅስቃሴ ገደቦች መካከል አንዳንዶቹን ከፊታችን ዕሁድ ጀምራ ልታነሳ መሆኑ ተዘግቧል።

በዚህም መሰረት የሃገር ውስጥ ጉዞ ክልከላው ይነሳል፤ መስጊዶች ለምዕመናን ክፍት ይሆናሉ፤ ምግብ ቤቶችም ይከፈታሉ ስትል አስታውቃለች።

የሳዑዲ መንግሥት ባወጣው መግለጫ መሰረት ከመካ ከተማ በስተቀር በተቀሩት የሃገሪቱ አካባቢዎች የጸኑት የእንቅስቃሴ ገደቦች በሙሉ ሰኔ ወር ውስጥ ይነሳሉ ብሏል።