ጠበቆቻቸውን ያላገኙ ተከሣሾች አሉ

አቶ አበበ ጉታ - የሕግ ጠበቃ

አቶ አበበ ጉታ - የሕግ ጠበቃ

ሰሞኑን በሙስና ተጠርጥረው የተከሰሱ ሰዎች ጠበቆች ዛሬ ደንበኞቻቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ተሰማ፡፡



Your browser doesn’t support HTML5

ጠበቆቻቸውን ያላገኙ ተከሣሾች አሉ



ሰሞኑን በሙስና ተጠርጥረው የተከሰሱ ሰዎች ጠበቆች ዛሬ ደንበኞቻቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ተሰማ፡፡

ስድስት ጠበቆች ዛሬ ከቀትር በኋላ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ በጥበቃ ሥር የሚገኙ ደንበኞቻቸውን ለማነጋገር ሄደው ከሁለት ሰዓት በላይ እስከሚሆን ጊዜ ቆይተው ሳያገኝዋቸው መመለሣቸውን ከጠበቆቹ አንደኛው ለቪኦኤ አመልክተዋል፡፡

ጠበቆቹ በጥበቃ ተሰላችተው ሊመለሱ ሲሉ ከተከሣሾቹ የሁለቱ ጠበቆች የሆኑት የዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ጠበቃ አቶ ዓለሙ ደነቀ እና የአቶ እሸቱ ወ/ሰማያት ጠበቃ አቶ ሲሣይ ለምለም ብቻ ደንበኞቻቸውን እንዲያነጋግሩ ዕድል የተሰጣቸው መሆኑን እኒሁ ጠበቃ አመልክተዋል፡፡

ይህ ሁኔታ የተፈጠረው ዛሬ ብቻ ሣይሆን ትናንትም እንዲሁ ሲጉላሉ ቆይተው ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ከትናንት በስተያ ማክሰኞ በሰጠው ውሣኔ ተከሣሾቹ ጠበቆቻቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ የሃይማኖት አባቶቻቸውን ማግኘት እንዲችሉ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሣል፡፡

በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት እና በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሠረትም ማንም እሥረኛ ጠበቃውን የማማከር መብት እንዳለው ተደንግጓል፡፡

የጠበቆቹን ስሞታ አስመልክቶ ከፖሊስ የሚሰጥን ምላሽ ለማግኘት በመጣር ላይ ነን፤ ባገኘን ጊዜ አካትተን እንመለሣለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡