ከህይወት ምን ይፈልጋሉ?

Your browser doesn’t support HTML5

ለመኖር ላቅ ያለ ዋጋ ማስገኘት ብቻ ሳይሆን፤ ትርጉም ያለው ኑሮ ለመኖር ጭምር መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ይመስላል።

“የሚያልቅ እና የማይደገም አንድ ህይወት መሆኑን ስናውቅ እንዲሁ በዘፈቀደ በልማድ ብቻ መኖር አንችልም” ይላሉ የአንጎል ሃኪሙ እና “አለመኖር” እና “አለማወቅ” የተባሉ ሁለት ከፍተኛ ተነባቢነት ያገኙ መጻህፍት ደራሲ የትንሳኤ ወግ እንግዳችን ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ።

በየትኛውም የእድሜ እርከን እና የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ያለን ማንኛውንም ሰው የሚመለከቱት እነኚህ ጥያቄዎች በዋናነት ለገዛ ራስ የሚቀርቡ ናቸው። ከወዳጅ፣ ጓደኛ አለያም ከቤተሰብ አባል ጋር ለመነጋገር መጋበዛቸውም አልቀረም።

እናስ ወድቆ ከመነሳቱ፣ ማለቂያ ያለው ከማይመስለው እና ከማይሞላው የእለት ኑሮ ደፋ ቀና ባሻገር በህይወትዎ ማድረግ የሚፈልጉት፣ ከሁሉ የላቀውን ሥፍራ የሚሰጡት ጉዳይ ምንድ ነው?

ከጥሞና ሃሳብዎ ሳይናጠቡ በርዕሱ ላይ የያዝነውን ወግ ይጋበዙ።