በኢትዮጵያ የችግኝ ተከላ ዘመቻዎች የሚሰሙ ውዝግቦች

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ፣ ላለፉት አራት ዓመታት የተካሔዱ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሮች፣ የተተከሉ ችግኞችን ቁጥር እና የጸደቁትን መጠን የሚያጠና ገለልተኛ የጥናት ተቋም ወደ ሥራ እንደገባ፣ የመርሐ ግብሩ የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ ዶክተር አደፍርስ ወርቁ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡ ችግኝ ተከላው፣ ከመንግሥት እጅ እየወጣ ወደ አርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ አዘቦታዊ ተግባር እየገባ እና ባህልም እየኾነ ነው፤ ብለዋል።

በዚኽ ሐሳብ የማይስማማው፣ በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሠራው ዮናታን ክብረት ካሳ በበኩሉ፣ የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እና ለችግኝ ተከላ የሚኾን አገራዊ የኢኮኖሚ እና የሰላም ኹኔታን መፍጠር፣ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፤ ይላል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ችግኝ ተከላ፣ ከዘመቻ አጀንዳ ባለፈ ባህል ኾኗል የሚል እምነት እንደሌለው ገልጿል።

ሙሉ ዘገባን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።