ፌብርዋሪ፤ በአሜሪካ የጥቁሮች ታሪክ ወር

Your browser doesn’t support HTML5

የጥቁሮች ታሪክ ወር (ብላክ ሂስትሪ መንዝ) በየዓመቱ ባሳለፍነው ወርኃ ፌብርዋሪ ይዘከራል፥ ይነገራል። ወሩ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ጉልህ ሥፍራ የነበራቸው ታሪኮች፣ የገነኑ ስሞችና ክንዋኔዎች ወይም እንደዋዛ የታለፉ ገፅታዎች የሚገባቸውን ትኩረት የሚያገኙበት ነው። ወሩን ጠብቀው ብቻም ሳይሆን የጥቁሮች ታሪክ ጎልቶ ዓመቱን ሙሉ እንዲነገር የሚታትሩ ደግሞ ብዙ ናቸው። የተያያዘው የአሜሪካና ህዝቧ ዘገባ ለቀደመ ታሪክ በአዲስ መንገድ ህይወት በመስጠት ሥራ ላይ ያሉ አንዲት ሴት ያስተዋውቀናል።