ደቡባዊዋ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ሀገር ቴኔሲ በአሜሪካ ሀገረ ሰብ ሙዚቃ ማዕከልነት ትታወቃለች፡፡ በርካታዎቹ እጅግ ዝነኛ የሆኑት የሀገሪቱ የሀገረ ሰብ ሙዚቃ ( Country Music) ክዋክብት የፈለቁት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቀው የቴኔሲው “Grand Ole Opry” የተባለው የሙዚቃ ትርዒት መድረክ ነው፡፡ ባንጆ የአብዛኞቹ የአሜሪካ ሀገረ ሰብ ሙዚቃ ቅንብር አካል ነው፡፡ የቪኦኤዋ ሌሺያ ባካሌትስ ሁለት የቴኔሲ የባንጆ ሠሪዎችን የዚህን መሰረቱ አፍሪካ የሆነ የሙዚቃ መሳሪያ ታሪክ እና ልዩ የሆነውን አሠራሩን ጠይቃቸዋለች፡፡
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።