የየኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ለረዢም ጊዜ ሲገፋ የቆየውን ብሄራዊ ምርጫ ትላንት እሁድ ማካሄድዋ የሚታውቅ ቢሆንም፣ የምርጫው ሂደት ግን የቅንብር ጉድላት፣ የድምፅ ማጭበርበርና የምርጫ መሣርያዎች በሚገባ ያለመሥራት ጉድለት መስተዋላቸው ተገልጧል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የየኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ለረዢም ጊዜ ሲገፋ የቆየውን ብሄራዊ ምርጫ ትላንት እሁድ ማካሄድዋ የሚታውቅ ቢሆንም፣ የምርጫው ሂደት ግን የቅንብር ጉድላት፣ የድምፅ ማጭበርበርና የምርጫ መሣርያዎች በሚገባ ያለመሥራት ጉድለት መስተዋላቸው ተገልጧል። በዚህም የተነሳ ብዙዎች የማይሰሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል በሚል መነቀፉ አልቀረም።
ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተወከሉ ታዛቢዎች በበኩላቸው፣ የድምፅ መስጫዎቹ አንጻራዊ ሰላም የታየባቸው ቢሁኑም፣ አካባቢው ግን ውጥርጥር ማለቱን፣ የኢንተርኔት አገልግሎቶችም ተሰናክለው መቆየቱን ገልጸዋል።
በፕረዚዳንታዊው ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኙት ሁለት ተወዳዳሪዎች በየበኩላቸው እንደሚያሸንፉ በእርግጠኛነት ተናግረዋል።
የምርጫውን ሂዳት የሚነቅፉ ሰዎች ግን በምርጫው ወቅት የተንጸባረቀው የቅንብር ጉድልት፣ ገዢው የጥምረት ፓርቲ ቁጥጥሩን እንዲያጠበቅ ሲባል ሆን ተብሎ የተደረገ ዕቅድ ነው እንደሚሉ ተመልክቷል።