የኮሌራ ወረርሽኝ በጎፋ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ለ አራት ሰዎች ሞት ምክንያቱ የኮሌራ ወረርሽኝ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ከዞኑ የተላከለትን ናሙና መርምሮ አረጋገጠ። አዲስ ሞት ባይመዘገብም ለወረርሽኙ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 153 መድረሱንና ቢሮው ከመንግስት መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት ወረርሽኙ ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይዛመት የመከላከል ስራ ማጠናከሩን አስታውቋል። የዞኑ ጤና መምሪያ ክልሉ መድሃኒትና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ገልጧል።