ቻይናውያን አሰሪዎች የሚፈጽሙት የመብት ጥሰት አፍሪካ ያላትን ገጽታ እያጎደፈው ነው?

Your browser doesn’t support HTML5

ሩዋንዳ ውስጥ አንድ የቻይና ኩባኒያ አሠሪ ከግንድ ጋር የታሰረ ሠራተኛን ሲገርፍ የሚያሳየው የቪዲዮ ምስል ከአፍሪካውያን አዕምሮ አልጠፋም። በአህጉሪቱ ዙሪያ ቁጣ ቀስቅሷል። የሩዋንዳ ፍርድ ቤት ድርጊቱን በሠራተኛው ላይ የፈጸመውን ሱን ሹጁን የተባለውን ቻይናዊ የማዕድን ቁፋሮ ሥራ አስኪያጅ የሃያ ዓመት እስራት ቅጣት ወስኖበታል። በአፍሪካ ሀገሮች ቻይናውያን አሠሪዎች ሠራተኞቻቸው ላይ የሚያደርሱት የማሰቃየት ድርጊት በስፋት የሚታይ መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡

ከደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ከተማ ኬት ባርትሌት ያጠናቀረችውን ሪፖርት ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡