አዲስ አበባ —
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የተገኙበትን ጨምሮ ከመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር የተደረጉ የምክክር መድረኮች ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡
ዛሬ፣ ሐሙስ - ታኅሣስ 17/2006 ዓ.ም አዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል የተካሄደውን የፌደራል መንግሥቱና የግሉ ዘርፍ ምክክር መድረክ አስመልክቶ ቪኦኤ ያነጋገራቸው የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሙሉ ሰሎሞን “እስካሁን በመፍትሔነት ካቀረብናቸው ነጥቦች ከ97 ከመቶ በላይ በመንግሥት ተቀባይነት አግኝተዋል” ብለዋል፡፡
“የውሣኔ ሃሣቦችን በማስፈፀም በኩልም የተወሰነ ርቀት ተኳዷል” ሲሉ አክለዋል የንግድና ዘርፍ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሙሉ፡፡
ለዝርዝሩ የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5