የአማራ ክልል ሰበር ሰሚ ችሎት ውሣኔ እንዳልተፈፀመ ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ

  • መለስካቸው አምሃ

ሰማያዊ ፓርቲ

Your browser doesn’t support HTML5

የአማራ ክልል ሰበር ሰሚ ችሎት ውሣኔ እንዳልተፈፀመ ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ

በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤትና በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ በምርጫ-2007 እንዳይወዳደሩ እገዳ ተጥሎባቸው የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ ስድስት ዕጩዎች በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ እግዱ ተነስቶላቸዋል።

ፍርድ ቤቱ ውሣኔውን ተግባራዊ እንዲሆን ተዕዛዝ ሰጥቷል።

ትዕዛዙ ግን እስከ ዛሬ ተግባራዊ እንዳልተደረገ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡