ቡሩንዲ ውስጥ በመንግሥት የሚታገዙ ሚሊሺያዎች በፕሬዚዳንት ፔር ኑኩሩዚዛ ተቃዋሚዎች ላይ የከፈቱት የሽብር ዘመቻ እየተባባሰና እየተስፋፋ መምጣት በብርቱ እንዳሳሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ተናገሩ።
ቡሩንዲ ውስጥ በመንግሥት የሚታገዙ ሚሊሺያዎች በፕሬዚዳንት ፔር ኑኩሩዚዛ ተቃዋሚዎች ላይ የከፈቱት የሽብር ዘመቻ እየተባባሰና እየተስፋፋ መምጣት በብርቱ እንዳሳሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ተናገሩ።
በማኅበራዊ ብዙሃን መገናኛ ላይ የሚዘዋወሩ የቪዲዮ ምስሎች የሰቆቃ ዘመቻውን ሰቅጣጭነት በግልፅ እንደሚያሳዩ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አስታውቋል፡፡
ከፍተኛ ኮሚሺነሩ ዛይድ ራ አድ አል ሁሴን ቃል አቀባይ ሩፐርት ኮልቪል ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ በመንግሥት የሚታገዙ የኢምቦኖራምኩሩ ወጣት ሚሊሻ አባላት ግጭት ሕዝብን ሲያነሳሱ የሚያሳይ ቪድዮ በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5