የኢራን የኑክሌር ሥምምነት

  • ቪኦኤ ዜና

European Union foreign policy chief Josep Borrell

ብሪታንያ፣ ፈረንሳይና ጀርመን ኢራን እአአ በ2015 የፈረመችውን የኑክሌር ሥምምነት እየተወች መሆኗን ገልፀዋል።

በሥምምነቱ ወቅት በተቀመጠው መሰረት ሁኔታውን ጠብን ወደ መፍታት ሂደት ከመውሰድ በስተቀር የቀረን አማራጭ የለም ብለዋል።

በጣምራው የተግባር ዕቅድ መሰረት ኃላፊነታችንን ተወጥተናል፤ በኢራን ላይ ተጥሎ የነበረውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ አንስተናል፤ ከሃገሪቱ ጋር ህጋዊ ንግድ እንዲካሄድም ጥረት አድርገናል ብለዋል ሀገሮቹ።

“ነገር ግን ኢራን ዋነኛ የሆኑትን ገደቦች መጣሱን ቀጥላለች” ይላል ሦስቱ ሀገሮች ያወጡት መግለጫ። የኢራን ተግባር የኑክሌር ሥምምነቱን ይፃረራል። ከባድ ሊስተካከል የማይችል አንደምታም ይኖረዋል ይላሉ።

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይናና ሩስያም የፈረሙት ሥምምነት ኢራን የኑክሌር መሳርያ እንዳትገነባ የሚያግድ መሆኑ ይታወቃል። ኢራን በልዋጩ ኢኮኖሚዋን ክፉኛ ጎድቶ የነበረው ማዕቀብ ተነስቶልታል።

ዩናይትድ ስቴትስ እአአ በ2018 ከሥምምነቱ ከወጣች በኋላ ግን ኢራን ሥምምነቱን ያለማክበር ዕርምጃ መውሰድ ጀመረች።