የብሪታኒያ የኢኮኖሚ ቀውስ

Your browser doesn’t support HTML5

የብሪታኒያ ኢኮኖሚ በሚቀጥለው ዓመት በ0 ነጥብ 4 ከመቶ እንደሚቀንስ ተገለጸ። ይህም ከባለጸጎቹ የቡድን -7 አባል ሀገሮች ከሁሉም ከፍተኛው መሆኑን የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት አስታውቋል። ከለንደን የአሜሪካ ድምጹ ሄንሪ ሪጅዌል እንደዘገበው ዓለም አቀፋዊው የምጣኔ ሀብት ይዞታ በሰሞኑን ከነበረው ፖለቲካዊ ትርምስ ጋር ተዳምሮ የእንግሊዝን ኢኮኖሚ እንደጎዳው ተንታኞች ይናገራሉ።