Your browser doesn’t support HTML5
ጥቃቱን “የሽብር ፈጠራ አድራጎት ነው” ሲሉ ዛሬ የጠሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ተጠያቂዎችን ለፍርድ እንደሚያቀርቡም ዝተዋል፡፡
በጥቃቱ አንድ የስምንት ዓመት ልጅን ጨምሮ ሦስት ሰው መሞቱና 176 ሰው መቁሰሉ ታውቋል፡፡ 17 ሰው ከባድና አሣሣቢ ነው በሚባል ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡
በትላንቱ የቦስተን ማራቶን ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች ተሣትፈው መሪ ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወቃል።
የድል ዜናው አስደሣች ቢሆንም የደረሰው አደጋ ደግሞ ሁሉንም አሣዝኗል፣ አሣስቧል፡፡
በአትሌቶቹ ላይ የተፈጠረ ችግር ካለ ከራሣቸው ለማጣራት ሞክረናል።
አትሊት ሌሊሳ ዴሲሳን ሰሎሞን ክፍሌ አነጋግሮታል