የአንበጣ መንጋን ለመከላከል ያቀረበው የአውሮፕላን ጥያቄ እንዳልተመለሰለት ኦሮምያ ክልል ጠቀየ

Your browser doesn’t support HTML5

ኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ውስጥ ተከስቷል የተባለውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ከኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስቴር የጠየቀውን የአውሮፕላን ድጋፍ አለማግኘቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። ግብርና ሚኒስቴር የተጠየቀውን አውሮፕላን ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን ገልፆ፤ የአንበጣ መንጋውን ለመቆጣጠርም ባለሞያዎችን ወደ ቦታው መላኩን አስታውቋል።