“ድርቁ ከብቶቻችንን ጨርሶ ባዶ እጃችን እያስቀረን ነው” የቦረና ዞን አርብቶ አደሮች

Your browser doesn’t support HTML5

ለሦስት ተከታትይ ወቅት ዝናብ አለመዝነቡን ተከትሎ በደቡብና በምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጫናውን አበርትቷል። በቦረና ዞን ያሉ አርብቶ አደሮች የኑሯቸው ምሰሶ የሆኑት ከብቶች በድርቁ ምክንያት በመሞት ላይ በመሆናቸው ባዶ እጃቸውን መቅረታቸው እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል። የዞኑ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኃላፊ በእስካሁኑ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ከብቶች መሞታቸውን ገልጿል።

የቦረና ዞን የእንስሳት ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት በበኩሉ የድርቁ ጫና ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን የሚል ስጋት እንዳለ ጠቁሟል።