በተቀበረ ፈንጂ ፍንዳታ አምስት ኢትዮጵያውያን ሞቱ

  • ግርማይ ገብሩ

በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር በሚገኘው ገርሁ ሰርናይ በተባለ አካባቢ መንገድ ላይ የተቀበረ ፈንጅ ፈንድቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ በነበረ አምቡላንስ አደጋ ማድረሱን፣ በአደጋውም የአምቡላንሱን አሽከርካሪ ጨምሮ፣ ሁለት ነፍሰ ጡር እናቶችና ሁለት ኃኪሞች በአጠቃላይ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ዘጋቢያችን ግርማይ ገብሩ የሟች ቤተሰብ አባላትን ጠቅሶ ዘገባ አድርሶናል።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የትግራይ ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ መኮንን አደጋው በተጠቀሰው አካባቢ መድረሱንና በአደጋውም አምስት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በተቀበረ ፈንጂ ፍንዳታ አምስት ኢትዮጵያውያን ሞቱ