ሰማያዊ ፓርቲ፣ የግንቦት 25ቱ ሰልፍ እና ወጣቶች

  • ቪኦኤ ዜና

የተቃውሞ ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ ተካሄደ




የተቃውሞ ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ ተካሄደ


Your browser doesn’t support HTML5

ሰማያዊ ፓርቲ፣ የግንቦት 25ቱ ሰልፍ እና ወጣቶች


ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃዋሚዎች በስምንት ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ግንቦት 25 ለሰልፍ አደባባይ ወጥተው ነበር።

ከተቀሩት የአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ሲነፃፀር አዲስ በሆነው ሰማያዊ ፓርቲ የተደራጀው የተቃውሞ ሰልፍ ኢህአዴግ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የፖለቲካ መድረኩን “ሰፋ ሊያደርግ ይሆን?” የሚል ተስፋ ፈንጥቋል።

የግንቦት 25ቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አደራጆች አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው፤ አብዛኞቹ የሚተዳደሩበት ሙያ አላቸው፣ እያቆጠቆጠ ላለዉ ሰማያዊ ፓርቲ ነፃ የድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡት ከሥራ በኋላ ማታ ነው።

የፓርቲው ደጋፊዎች ለሰላማዊ ሰልፉ ዝግጅት ያደርጉ በነበረ አንድ ምሽት በቢሯቸው ተገኝታ ዘጋቢአችን ማርቴ ፋን ደር ቮልፍ አነጋግራቸው ነበር፡፡

ምን ዉጤት እንደሚጠብቁ ጠይቃቸዋለች።

ዝርዝሩ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡