የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት በቡለን ወረዳ ታስረው መለቀቃቸውን አስታወቁ

  • እስክንድር ፍሬው

አቶ ይልቃል ጌትነት - የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች የሚገኙበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መግለፃቸውን ቀጥለዋል፡፡



ቤንሻንጉል-ጉምዝ


Your browser doesn’t support HTML5

የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ቤንሻንጉል ጉምዝ ውስጥ ታስረው መለቀቃቸውን አስታወቁ


የቤንሻንጉል-ጉምዝ ወረዳዎች

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች የሚገኙበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መግለፃቸውን ቀጥለዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ


ወደ ቡለን ወረዳ በመጓዝ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ተመልክተው መመለሣቸውን የተናገሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት “ችግሩ አሁንም አልተቀረፈም” ብለዋል፡፡

የወረዳው አስተዳዳሪ ግን “ስለአርሦ አደሮቹ እየተሠራጩ ያሉት ወሬዎች የተሣሣቱ ናቸው” ይላሉ፡፡ ፌደራሉ መንግሥት በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በሰጡት መግለጫ ደግሞ “ሁኔታው የወረዳው አስተዳዳሪ ከሰጡት መግለጫ የተለየ ነው” ብለዋል፡፡

አቶ ይልቃል ጌትነት - የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር


እርሣቸውና ሌሎችም የፓርቲያቸው አመራር አባላት ለአምስት ሰዓታት በወረዳው ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበረና በምሥል የያዟቸው ማስረጃዎች በፖሊስ አባላቱ እንደተሠረዙባቸው አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያዳምጡ፡፡