“እስራኤል እና ፍልስጤም በሰላም የሚኖሩበት መፍትሄ ግድ ነው” ብሊንከን

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከትላንት በስቲያ እሁድ እና ትላንት ሰኞ ግብፅን እና እስራኤልን በጎበኙበት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ይህ ገለጻቸው የተሰማው በአካባቢው የሚታየው ብጥብጥ በቀጠለበት እና ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመሆን የያዘችውን ጥረት አስመልክቶ ያለው ስጋት እየጨመረ በመጣበት ወቅት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ: ብሊንከን በዛሬው ዕለት ወደ ዌስት ባንክ ከማምራታቸው አስቀድሞ በእስራኤል እና በአረብ ሃገሮች መካከል ሰላማዊ ግንኙነት ለመፍጠር ስለተደረጉት ስምምነቶች አስፈላጊነት አጽንኦት በሰጡበት አስተያየት፤ ሁለቱን አገሮች .. እስራኤልን እና ፍልስጤምን በሰላም ለመኖር የሚያስችል መፍትሄ ስለሚያማጣ እድልም ተናግረዋል።