ታዋቂው የብሄራዊ የአሜሪካ እግር ኳስ (ፉትቦል) ሊግ አሰልጣኝ አንተኒ ሊን፣ ሊጉ እጩዎች አንስተኛ ቁጥር ካላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለአሰልጣኝነት እንዲመለመሉ ለቃለመጠይቅ የሚጋብዝ ፖሊሲ ያለው በመሆኑ ደስተኛ ነው፡፡ እሱም ቢሆን የዚህ እድል ተጠቃሚ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ግን፣ የሳንፍራንሲስኮው ቡድን ረዳት አሰልጣኝ፣ እሱም ልክ እንደ ባልደረቦቹ ሁሉ፣ ፖሊሲው አሁንም ብዙ የሚቀረው መሆኑን ያምናል፡፡
ፖሊሲው ተግባራዊ በሆነበት እኤአ በ2003 ከነጭ ውጭ የነበሩት አስልጣኞች ቁጥር ሶስት የነበሩ ሲሆን ዛሬ አምስት ናቸው፡፡
ቁጥሩ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ከፍና ዝቅ ሲል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ስለ ብሄራዊ ሊጉ የቅጥር ሁኔታ በንኡሳኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ አሁንም ቅሬታው እንዳለ ነው፡፡
ቀደም ሲል የሊጉን የተዋጽኦ ኮሚቴውን ሲያስተባበር በነበረው በስቲለር ቡድን ባለቤት ዳን ሩኒ ስም የተሰየመው የሩኒ ህግ ከወጣ በኋላም ቢሆን ቅሬታው እንደቀጠለ ነበር፡፡
ጥቁሩ ሊን፣ በሩኒ ህግ ላይ የራሱን የግል ማሻሻያ ህግ ካከለበት ቆይቷል፡፡ እኤአ በ2010 እንደ ረዳት አሰልጣኝ ዝናው በናኝበት ጊዜ ሊን ከቡድኖች ጋር የሚገናኘው ለዋና አሰልጣኝነት ክፍት በሆኑ የሥራ መደቦች ዙሪያ ለመወያየት ብቻ ነው፡፡
ለአሼዬትድ ፕሬስ ሲናገር ዝምብሎ ለወሬ ብቻ የሚሆን ቃለ መጠይቅ አልፈልግም ነበር ብሏል፡፡
“በሩሊ ህግ መንፈስ በትክክል አምናለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ግን ሰዎች ህጉን እንዴት እንደሚጥሱት አውቃለሁ እኔ የዚያ አካል መሆን አልፈልግም” ሲል ተነግሯል፡፡
በዚህ ወር በቀድሞ የማያሚ ዶልፊን ዋና አሰልጣኝ ብራያን ፍሎረስ በበርካታዎቹ የብሄራዊ እግር ኳስ ሊግ ቡድኖች ላይ የተመሰረተው የዘር መድልዎ ክስ የሊጉ የቅጥር አሰራሮችን አጉልቶ አሳይቷል፡፡
በሩኒ ህግ ተግባራዊ ያልተደረጉባቸው በርካታ ቅሬታዎችንም ግልጽ አድርጓል፡፡ እንዲሁም በሊን እና በሌሎች የአሜሪካ ኩባንያዎች መካከል ያለውን ንጽጽር በማሳየት ከፍተኛ የአመራር አካላት ስብጥር ጉድለት አሳይቷል፡፡
የሊን ጽናት፣ እኤአ በ2017 የሎስ አንጀለስ ቡድን በቡድኑ ታሪክ የመጀመሪያው ጥቁር ዋና አስልጣኝ አድርጎ ሲሾመው ከፍሎታል፡፡
እጩው ሊን ካሸነፋቸው ተፎካካሪዎች መካከል አሁን የስቲለርስ ተከላካይ አስተባባሪ የሆነው ቴሪል ኦስትን ይገኝበታል፡፡
ኦስትን ወደ 11 ጊዜ ከዳኞቹ ዘንድ ፊት ለፊት ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እድሉን ያገኝ ቢሆንም የዋና አሰልጣኝነት ሥራውን ግን ሊያገኝ አልቻለም፡፡
ኦስተን በወቅቱ እየተፎካከረ መሆኑ ቢሰማውም ይሁን እንጂ የህጉንም መስፈርቶች ለማሟላት መመዘኛዎችን ቅጽ የሚሞላ መስሎት ነበር፡፡
የኦስተን የግል ገጠመኝ በፎሎረስ የህግ ክስ ውስጥ የተካተተ ሲሆን፣ አሰራሩ ብቁ ሥራ ፈላጊዎችን በሚጥል አድልዎ የተሞላ ስለመሆኑ እንደማረጋጋጭ ሆኖ ቀርቧል፡፡
የብሄራዊ እግር ኳስ ሊጉ ኮሚሽነር ሮጀር ጉዴል፣ “ሊጉ በብዙ መልኮች ብዙ መሻሻሎችን አሳይቷል” በማለት ከፊሉን ክስ አስተባብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ዋና አስልጠኞን በሚመለከት ሊጉ ወደ ኋላ መቅረቱን አምነዋል፡፡
ጉዴል ከእሁዱ ሱፐር ቦል በፊት በሰጡት መግለጫ “የምንሰራቸው ተጨማሪ ሥራዎች አሉን፡፡ እነዚያን ለይተን ማወቅ ይኖርንብናል፡፡” ብለዋል፡፡
ብሄራዊ ሊጉ የውጭ ኤክስፐርቶችንም የቅጥር ፖሊሲዎችን በመገምገም በጉዳዩ ላይ ማሳተፍ መጀመሩንም ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የሩኒ ህግ ሳይሻር ሊቀጥል ስለሚችልበት ሁኔታ ማረጋገጫ አልሰጡም፡፡
በዚህ ዓመት ለሱፐር ቦል የሚፋለሙ ሁለቱ የሲንሲናቲው ቤንጋልስ እና የሎስ አንጀለሱ ራምዝ አጥቂ አስተሳሰብ ባላቸውና በሰላዎቹ እድሜ ውስጥ ባሉ ሁለት ነጮች ዋና አስልጣኝነት የሚመሩ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የነሱን የማጥቃት የመከላከልና የልዩ ቡድን የሚገመግሙ በርካታ የተሰባጠሩ የማህበረሰብ ክፍሎች አሉ፡፡
ለራምዝ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሚሰሩ በርካታ ንኡስ አሰልጣኞች መካከል ግማሾቹ ጥቁሮች ናቸው፡፡
የአሁኑ የስትሌር ፕሬዚዳንትና የዳን ልጅ የሆነው አርት ሩኒ ሁለተኛ፣ የአባታቸውን የቅጥር ፖሊሲ በመከላከል ተሟግተዋል፡፡
አርት ሩኒ “ምንም እንኳ በዋና አሰልጣኞች ረገድ ለውጥ ባናይም ሴቶችና የንኡሳን ማህበረሰብ አባላትን ቁልፍ በሆኑ የአመራር ቦታዎች በመቅጠር ተጨባጭ ለውጥ አሳይተናል፡፡” ብለዋል፡፡
በርግጥ በብዙ ቦታዎችም ወደ ላይ እንጂ ወደየትም መሄድ አይቻልም ነበር፡፡
ብሄራዊ የ እግር ኳስ ሊጉ የሚታዩ በርካታዎቹን የአመራር ስፍራዎችን በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ለማሰባጠር መንገድ ጀምሯል፡፡ ከረዳት አሰልጣኞች ውስጥ አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት ጥቁሮች ናቸው፡፡ በዚህ የጨዋታ ሰሌዳ ውስጥ እንኳ ሁለት ጥቁር አጥቂ አስተባባሪዎች ነበሯቸው፡፡ እነዚህ ዋናው የአሰልጣኝነት ስፍራ ከመያዝ በፊት የሚመጡ መደቦች ናቸው፡፡ የማህበራዊ ስብጥርና የስፖርት ስነምግባር ተቋም ባወጣው ሪፖርት መሰረት ወደ 85 ከመቶ የሚቆጠሩ የሊጉ ዋና ሥራ አስኪያጆች የተጫዋቾች ፐርሶኔል ዳይሬክተሮች ነጮች ናቸው፡፡
የቀድሞ የአሜሪካ እግር ኳስ ተጫዋችና ብሄራዊ እግር ኳስ ሊጉ የኦፕሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ቶኒ ቪንሰንት “ይህ የፈቃደኝነትና የልብ ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡
“ሰዎችን ማስገደድ አትችልም ስለዚህ ማተማርና በቅጥር ሂደቱ ውስጥ ለሚያልፉት ሁሉ ያንን ማስተላለፍ አለብን” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
“ተጨዋቾም ለውጡን እንዲመጣ በማድረግ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው” ያሉት ደግሞ የማህበራዊ ስብጥርና የስፖርት ስነምግባር ተቋም ድሬክተር ሪቻርድ ላፕቺክ ናቸው፡፡
ላፕቺክ የአሜሪካ ብሄራዊ ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች በማህበረሰብ አንቂነት ትልቁን ስፍራ የሚይዙ ናቸው ብለዋል፡፡
30 ከሚደርሱት የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ (ባስኬት ቦል) ቡድኖች መካከል፣ ግማሽ የሚሆኑት በጥቁር አሰልጣኞች የሚመሩ ሲሆን ከአንድ አራተኛ በላይ የሚሆኑ ዋና ስራ አስኪያጆች ጥቁሮች ናቸው፡፡፡
“እኔ የብሄራዊ እግር ኳስ ሊጉ አባላት በራሳቸው ይህን ተግባራዊ ያደርጋሉ ብዬ አልጠብቅም፡፡” ይላሉ ላፕቺክ፡፡ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው ስፖርተኞቹ ራሳቸው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ማሰማት ሲጀምሩ ነው፡፡ አስፈላጊ ነው ማለት አለባቸው፡፡” ብለዋል፡፡
በጥቅሉ ሲታይ 70 ከመቶ የሚሆኑት የብሄራዊ እግር ኳስ ተጫዋቾቹ ጥቁሮች ናቸው፡፡
አሜሪካ መሮቹ ኩባንያዎች (ኮርፖሬት አሜሪካ) ልክ እንደ ብሄራዊ የእግር ኳስ ሊግ ሁሉ የተሰባጠረውን የማህበረሰብ ክፍል በማቀፍ የራሳቸው ፈተናና የህግ ችግር አለባቸው፡፡
የሳንፍራንሲስኮው አሰልጣኝ ሊን “ ብሄራዊ የእግር ኳስ ሊጉ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል የተለየ አይደለም” በማለት እንዲህ ይላሉ
“ለምሳሌ የአሜሪካ ፎርቹን 500 የሚባሉትን ድርጅቶች ተመልክቱ፡፡ ከኛ ጋር ሲነጻጸር ምን ያህሉ ሥራ አሰፈጻሚዎች ከንኡሳኑ የማህበረሰብ ክፍል የሆኑ አሉባቸው? በመቶኛ ሲሰላ ምናልባት የኛ የተሻለ ሊሆን ይችላል፡፡”
በማህበራዊ ስብጥርና የስፖርት ስነምግባር ተቋም መረጃ መሰረት፣ ከ90 ከመቶ በላይ የሚሆኑት የፎርቹን 500 ፕሬዚዳንትና ሥራ አስፈጻሚዎች ነጮች ሲሆኑ፣ ጥቁሮቹ 3ከመቶ ብቻ ናቸው፡፡
የቀድሞ የሞርጋን ስታንሊ ዋነኛው የተዋጽኦና ስብጥር ድሬክተር ማርሊን ቡከር እኤአ በ2020 ባንኩን በዘር መድልዎና ክስ መስርተውበታል፡፡ በነጭ ሥራ አስፈጻሚዎች የተጥለቀለቀውን ድርጅት የማኔጅመንት ወይም የአመራር መደቡን ለማሰባጠር የነበራቸውን እቅድ ውድቅ ያደረጉባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሁለቱም ወገኖች ጉዳያቸው ከፍርድ ቤት ውጭ ባደረጉት ስምምነት ቋጭተውታል፡፡
ባላፈው ዓመት፣ አምስቱ ትላልቅ ባንኮች ጄፒ ሞርጋን ቼዝ፣ ባንኮ ኦፍ አሜሪካ፣ ሲቲ ግሩፕ፣ ዩኤስ ባንኮርፕ እና ዌልስ ፋርጎ የሩኒ ህግን “(የብሄራዊ የእግር ኳስ ሊጉን) በየድርጅታቸው ተግባራዊ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ስምምነቱን ያቀናጀው ድርጅት ቃል አቀባይ አስታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ባለሙያዎች እንደሚሉት ብዙዎቹ ድርጅቶች አሁንም ብዙ መስራት የሚገባቸው መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
ብዙዎቹ ድርጅቶች እንዲህ ዓይነቱን የተዋጽኦ ሚዛን ለመጠበቅ ተዋጽኦ፣ ፍትሃዊነትና አካታችነት የተሰኙት ቁልፍ ቃላት በማጣመር ለመስራት እየሞከሩ መሆኑን የሥራ አመራርና ትምህርት ቤት መምህሩ ኒኮላስ ፒርስ ተናግረዋል፡፡
በስፖርትም ሆነ በቢዝነስ ዘርፍ ያሉትን አግላይነት ማስወገድ ከተፈለገ፣ ቀጣሪ አካላትን ስብጥር በማስተካከልና የሥራ ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉትን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል በማድረግ ማቃናት ይቻላል ባይ ናቸው፡፡
የህዝብ ንብረት ከሆነው የግሪን ቤይ ፓከርስና እንዲሁም ከጃክሰን ቪል ሻድ ካን እና ባፍሎ ኪም ፒጉላ በስተቀር፣ ሁሉም ብሄራዊ የእግር ኳስ ሊግ ቡድኖች በነጮች የግል ይዞታ ስር የሚገኙ ናቸው፡፡
ለኒው ኢንግላንድ የተከላካይ መስመር አሰልጣኝ የሆነው የሆነው የ35 ዓመቱ ጄሮድ ማዮ አንድ ቀን ዋና አሰልጣኝ መሆንን ይመኛል፡፡
ጥቁሩ ማዮ እሱ ዝግጁ በሚሆንበት ጊዜ እንደ ሊን ኦስትንና ፍሎረስ ያሉት አንጋፋዎቹ ወደ ታሪክ ማህደር ይሸጋገራሉ፡፡ እንዲህ አለ ማዮ
“ምን እንደሚሆን ታውቃለህ ያ ውብ ቀን የሩኒ ህግን የማንፈልግበት ቀይን ይሆናል፡፡”