ወደ ማንነትን ፍለጋ- ሄለን ኬነርድ ወ/ት ኢትዮጵያ ዩናይትድ ስቴትስ

ሄለን ካነርድ ወ/ት ኢትዮጵያ ዩናይትድ ስቴትስ

የዘንድሮዋ ወ/ት ኢትዮጵያ በዩናይትድ ስቴትስ በትውልድ ስሟ ሔለን ወርቁ አሁን ደግሞ ሔለን ኬነርድ ትባላለች። የ29 ዓመት ወጣት ስትሆን፤ የተወለደችው ሆለታ ከተማ ነበር።

ሰባት ዓመት ሲሞላት ብቻዋን ልጆች ማሳደግ የከበዳት እናቷ እሷንና ሁለት እህቶቿን በማደጎ ለአሜሪካውያን አሳዳጊዎች ሰጠቻቸው። እሷና ታላቅ እህቷን አንድ ቤተሰብ ሲወስዳቸው አንድ እህቷን ደግሞ ሌላ ቤተሰብ ወሰዳት።

ሄለን ኬነርድ ወ/ት ኢትዮጵያ ዩናይትድ ስቴትስ

ሄለን ከቆይታ በኋላ የማንነት ጥያቄ ክፍተት ሲፈጥርባት ወላጆቿን ፍለጋ ተመልሳለች። ወላጆቻቸውን ያጡና በድሕነት ምክንያት መማር ያለቻሉ ሃያ አምስት ተማሪዎች ከቤተሰቦቿ ጋር ኾና ትረዳለች።

ሙሉ ታሪኳን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ወደ ማንነትን ፍለጋ- ሄለን ኬነርድ ወ/ት ኢትዮጵያ ዩናይትድ ስቴትስ