ዋይት ሓውስ ዐዲስ የድንበር ፖሊሲውን ለማሳመን እየጣረ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ፍልሰተኞችን ከድንበር ላይ ይዞ ወደመጡበት አገር የሚመልሰውና፣ በትረምፕ ዘመን የወጣው “ታይትል 42” የተሰኘው ደንብ፣ ትላንት ኀሙስ እኩለ ሌሊት ላይ በማብቃቱ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ፍልሰተኞች፣ በአሜሪካ ደቡብ ድንበር በኩል እንደሚጎርፉ በመጠበቅ ላይ ነው፡፡ “ታይትል 42” በተሰኘውና በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በወጣው ደንብ መሠረት፣ 2ነጥብ8 ሚሊዮን ስደተኞቸ ከድንበር ላይ ተይዘው ወደየመጡባቸው ሀገራት ተመልሰዋል፡፡

የቪኦኤዋ አኒታ ፓወል ከዋሽንግተን ያጠናቀረችውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ያቀርበዋል፡፡