የፖለቲካ ብጥብጥ መጪውን የዩናይትድ ስቴትስ አጋማሽ ጊዜ ምርጫ የደቀነው ፈተና

Your browser doesn’t support HTML5

የምርጫ አስፈፃሚ ሰራተኞች በመምረጫ ሥፍራዎች ከፍተኛ የስሜት መለዋወጥ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል መገመታቸው እና በቅርቡ በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፔሎሲ መኖሪያ ቤት የተፈፀመው ጥቃት ለዚህ ማሳያዎች ናቸው።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ሌሎች ታላላቅ የፖለቲካ ሰዎች የፔሎሲን ባለቤት፣ ፖልን ክፉኛ ያቆሰለውን ጥቃት በማውገዝ ህዳር ስምንት የሚካሄደው ምርጫ መቃረቡን ተከትሎ ሊቀሰቀስ የሚችል የፖለቲካ ሁከት እንዲቆም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።