ለቤኒሻንጉል ክልል መልሶ መቋቋም ከ38 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ተባለ

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፉት ሁለት ዓመታት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በነበረው የፀጥታ ችግር የደረሰውን ጉዳት ለመቀልበስና እና መልሶ ለማቋቋም ከ38 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የክልሉ መንግሥት ገለጸ።

የክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ "በሦስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ውስጥ የወደሙ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባትና ለማደስ ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ይወስዳል" ካሉ በኋላ ለተግባራዊነቱም ኅብረተሰቡ፣ መንግሥትና የተለየዩ የግብረ ሠናይ ድርጅቶች በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

ከክልሉ ተፈናቅለው ከነበሩ 475 ሺ ሰዎች መካከል እስከ አሁን ከ265 ሺ በላይ የሚሆኑ ወደየአካባቢያቸው መመለሳቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።

በክልሉ የሚንቀሳቀሰው "ቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ" የተባለው ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት "በክልሉ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች ለደረሰው ጉዳት የተሰጠው ትኩረት፣ አናሳ ነው" ሲል አስታውቋል።