የደኅንነት ስጋት የገባቸው የግልገል በለስ ከተማ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው አልተመለሱም

Your browser doesn’t support HTML5

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ፣ ከሦስት ሳምንታት በፊት ተፈጥሮ በነበረው ግጭት፣ ከአካባቢያቸው የተሰደዱ ነዋሪዎች፣ እስከ አሁን አለመመለሳቸውን ገለጹ፡፡

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ፣ ከሦስት ሳምንታት በፊት ተፈጥሮ በነበረው ግጭት፣ ከአካባቢያቸው የተሰደዱ ነዋሪዎች፣ እስከ አሁን አለመመለሳቸውን ገለጹ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮቹ፣ እስከ አሁን ወደ ቀዬአቸው ያልተመለሱት፣ ከሳምንታት በፊት ጥቃት የፈጸሙባቸው ታጣቂዎች፣ በዚያው በግልገል በለስ ከተማ በመኖራቸው እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።