የኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ ዘጋቢ ሙሉቀን ተስፋሁን ቤንሻንጉል-ጉምዝ ውስጥ ለሰባት ቀናት ታስሮ ከቆየ በኋላ ዓርብ ግንቦት 23/2005 ዓ.ም ተፈትቷል፡፡ የታሠረበት ምክንያት በሥርዓት አልተገለፀለትም፡፡
አዲስ አበባ —

ከግንቦት 16/2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 23/2005 ዓ.ም በአንድ የክልሉ እሥር ቤት ውስጥ እንዲቆይ የተደረገው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ዓርብ ከጠዋቱ 5 ሰዓት ላይ የተለቀቀው በዋስ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሙሉቀን ለቪኦኤ በስልክ በሰጠው ቃል የተሠረበትን ምክንያት በአግባቡ ያስረዳው ባይኖርም መጀመሪያ በቁጥጥር ሥር ያዋሉትን “የማኅበረሰብ ፖሊስ” አባላት “ለምንድነው የምታስሩኝ?” ብሎ ሲጠይቃቸው የሰጡት መልስ “የሰው ክልል ዘው ብለህ የገባኸው ለምንድነው?” የሚል እንደነበር ገልጿል፡፡
ከአማራ ክልል ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለመግባት “ኢትዮጵያዊነቴ ብቻ በቂ ነው” ቢላቸውም እነርሱ ግን ይህ ብቻ በቂ እንዳልሆነና መብቱ የተገደበ እንደሆነ ሊያስረዱት መሞከራቸውን ሙሉቀን አብራርቷል፡፡
ለጥቂት ጊዜም የፊጥኝ እንደታሠረና ሊያንገላቱትም ሞክረው እንደነበረ ተናግሯል፡፡
ለአምስት ቀናት ያህል መጀመሪያ በተያዘበት በቡለን ወረዳ ዶቢ እሥር ቤት ከቆየ በኋላ ወደ ግልገል በለስ ዞን ጣቢያ ሲላክ በጨረፍታ ያየው የመሸኛ ደብዳቤ “ፀጉረ-ልውጥ ሰውን ስለመላክ” የሚል እንደነበረ ሙሉቀን አመልክቷል፡፡
ሲያነብብ የነበረውን “የኢሕአዴግ ፍፃሜ” የሚል መፅሐፍ የተመለከተው ኢንስፔክተር ካሣሁን የሚባል መርማሪ ፖሊስ አባል “ለምን ልማታዊ መፅሐፋ አታነብብም? ይህ በእኛ ክልል እንዲነበብ አይፈቀድም” በማለት እንደገሠፀው ሙሉቀን ተናግሯል፡፡
በመጨረሻም ወደ አሶሣ ተዛውሮ ከክልሉ ፕሬዚዳንት በተፃፈ ደብዳቤ በወንድሙ በጌትነት ተስፋሁን ዋስትና እንደተፈታ ገልጿል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5